በመሰረታዊ ሸቀጦች ስርጭት እና አቅርቦት ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ዘመናዊ አሰራርን በመከተል ለመቅረፍ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አስታወቀ

You are currently viewing በመሰረታዊ ሸቀጦች ስርጭት እና አቅርቦት ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ዘመናዊ አሰራርን በመከተል ለመቅረፍ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አስታወቀ

AMN – ግንቦት 21/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የንግድ፣ የኢንዱስትሪና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮን የስራ እንቅስቃሴ ተመልክቷል፡፡

ቢሮው ገበያን በማረጋጋት ሂደት አበረታች ስራዎች መስራቱን በመስክ ምልከታ ማረጋገጥ መቻሉን የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ጋትዌች ዎር ገልጸዋል።

ይህንኑ አጠናክሮ ለማስቀጠል አቅርቦት እና ስርጭት ላይ በትኩረት መስራት እንዳለበትም ሰብሳቢው አሳስበዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው የአሰራር ስርዓትን ለማሻሻል የሚያግዝ የህግ ማዕቀፎች ተግባራዊ እንዲሆኑ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግም ሰብሳቢው ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በበኩላቸው፣ ቀደም ሲል ከማህበረሰቡ ይነሱ የነበሩትን በመሰረታዊ ሸቀጦች ስርጭት እና አቅርቦት ላይ ያሉ ቅሬታዎችን ዘመናዊ አሰራርን በመከተል መቅረፍ እንደተቻለ ገልጸዋል።

ቢሮው በኦላይን የሚካሄድ ሕገ ወጥ ንግድ፣ አዋኪ ድርጊት ላይ የተሰማሩ የንግድ ተቋማት ላይ ዘላቂ መፍትሔ እንዲመጣ በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባው የቋሚ ኮሚቴ አባላትም አስተያየት ስጥተዋል።

የምርት እጥረት ሳይኖር የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ጥቂት ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር እና ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ሕዝቡ አሁንም ከቢሮው ጎን እንዲቆም የቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ጥሪ አቅርበዋል።

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review