በመዲናዋ ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 5 ነጥብ 2 ሚሊየን ችግኞች ተዘጋጅተዋል

You are currently viewing በመዲናዋ ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 5 ነጥብ 2 ሚሊየን ችግኞች ተዘጋጅተዋል

AMN – ግንቦት 22/2017 ዓ.ም

ዘንድሮ ለሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 5 ነጥብ 2 ሚሊየን የውበት፤ የጥላ እና ለምግብነት የሚውሉ ችግኞች መዘጋጀታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግርማ ሰይፉ ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ባለፉት ስድስት አመታት በተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሮች በሚሊየን የሚቆጠሩ የተለያዩ ችግኞች መተከላቸውን ገልጸዋል።

በዚህም የከተማዋን የአረንጓዴ ሽፋን ከፍ በማድረግ ረገድም ትልቅ ስራ መሰራቱን ነው የገለጹት።

ለዘንድሮው መርሐግብርም 5 ነጥብ 2 ሚሊየን የጥላ፤ የውበት እና ለምግብነት የሚውሉ ችግኞች መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል፡፡

በከተማዋ ለሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ውሃን መልሶ በመጠቀም ለማጠጣት እንደሚውል የገለጹት የቢሮ ኃላፊው ይህን ይበልጥ በማጠናከር ለማስቀጠል እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

በመንገድ አካፋዮች ላይ የተተከሉ አረንጓዴ ቦታዎችን በመንከባከብ ረገድ ህብረተሰቡ እያደረገ ያለው አስተዋጽኦ የሚበረታታ ነው ያሉት አቶ ግርማ ሰይፉ በቀጣይም በሚከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡

በዝናሽ ሞዲ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review