በመዲናዋ በስፋት እየተገነቡ ያሉ የተሽከርካሪ ማቆሚያና ተርሚናሎች የትራንስፖርት አገልግሎቱን የማዘመን አካል መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ

You are currently viewing በመዲናዋ በስፋት እየተገነቡ ያሉ የተሽከርካሪ ማቆሚያና ተርሚናሎች የትራንስፖርት አገልግሎቱን የማዘመን አካል መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ

AMN- ግንቦት 13/2017 ዓ.ም

በመዲናዋ በስፋት እየተገነቡ ያሉ የተሽከርካሪ ማቆሚያና ተርሚናሎች የትራንስፖርት አገልግሎቱን የማሻሻልና የማዘመን አካል መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡

ከንቲባዋ ከ1 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚያስችለውን የየካ 2 የተሸከርካሪ ማቆሚያ መርቀው አገልግሎት አስጀምረዋል፡፡

በምረቃ መርሃ ግብሩ መልእክት ያስተላለፉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ የተሽከሪካሪ ማቆሚያዎችና የትራንስፖርት ተርሚናሎችን ለማስፋፋት የምናደርገው ጥረት የህዝባችንን ኑሮ ለማሻሻል የምናደርገው ስራ አካል ነው ብለዋል፡፡

ዘመናዊ የመኪና ፓርኪንግ አገልግሎት የዘመነ አስተሳሰብ ምንጭ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች ለዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያልተለመደ እና በአዲስ እሳቤ በከተማዋ በስፋት እየተተገበረ ያለ ተግባር ነው ብለዋል፡፡

በመገናኛና ሾላ መካከል የተገነባው የየካ 2 የተሽከሪካሪ ማቆሚያም የአካባቢውን የትራፊክ ፍሰት የሚያሳልጥ የንግድ እንቅስቃሴውን በማሻሻል ጠቀሜታው ከፍ ያለ መሆኑን ነው ከንቲባዋ የተናገሩት፡፡

የትራንስፖርት አገልግሎትን ማዘመንና ማሻሻል የብልጽግና ጉዟችን መሰረት ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች የከተማ አስተዳደሩ ከለውጡ ወዲህ ዘርፉን ለማሻሻል ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የከተማዋ ነዋሪ የትራንስፖርት ጫናን የመቀነስና ዘመናዊ አገልግሎት የመስጠት አካል የሆኑት የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎቹ የህብረተሰቡን ደህንነትና ክብር የሚያስጠብቁም ናቸው ብለዋል ከንቲባዋ ፡፡

በፍቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review