AMN-የካቲት 12/2017 ዓ.ም
የከተማዋን የቤት አቅርቦት ለማሻሻል በተለያዩ መርሃ-ግብሮች 27 ሺ 304 ቤቶች መገንባታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
ከንቲባ አዳነች ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለጹት፣ የከተማዋን የቤት አቅርቦት ፍላጎት ለማሟለት በመንግስት አስተባባሪነት፣ በሪል ስቴት እና በግል አልሚዎች በተለያዩ መርሃ-ግብሮች 27 ሺ 304 ቤቶች ተገንብተው የቤት አቅርቦትን መጨመር ተችሏል፡፡

በልዩ ልዩ የቤት አቅርቦት አማራጮች 120 ሺ ቤቶች ግንባታ ፕሮግራም የተጀመረ መሆኑን የገለጹት ከንቲባዋ ከተጠናቀቁት ውስጥ በከተማዋ ለሚሰሩ የህዝብ ልማት ስራዎች ለሚነሱ የልማት ተነሺዎች እና የተለያዩ ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች 9 ሺ 20 ቤቶችን ማስተላለፍ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል ህገ-ወጥነትን ለመከላከል 113 የጋራ መኖሪያ ቤት፣ 71 የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤት እና 172 የቀበሌ ቤት ማስለቀቅ መቻሉን አስታውቀዋል።
በወርቅነህ አቢዩ