የፖሊስ አሠራርና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ማነቆ የነበሩ ችግሮችን በማስወገድ እና በፖሊሳዊ ሥነ-ምግባርና ዲስፒሊን የወንጀል መከላከልና ምርመራ ስራዎቹን በቴክኖሎጂ በማዘመን የከተማውን ሠላም በዘላቂነት ማስቀጠል እንደተቻለ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ ተናግረዋል፡፡
ከመጋቢት ወር አጋማሽ ጀምሮ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አመራርና አባላት በተለያዩ ዙሮች ሲሰጥ የቆየው ግምገማዊ ስልጠና መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል ገልጸዋል፡፡
አልፎ አልፎ ከህዝብ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መመለስ እና የአገልግሎት ፈላጊውን ህብረተሰብ እርካታ መጨመር ተቋሙ በትኩረት እየሰራበት የሚገኝ ጉዳይ በመሆኑ ግምገማዊ ስልጠናው ይህንኑ ታሳቢ ያደረገ እንደነበርም አብራርተዋል፡፡
ፖሊስነት በፍፁም ታማኝነትና ስነ-ምግባር ማገልገልን የሚጠይቅ ሙያ በመሆኑ፣ በአንዳንድ አመራርና አባላት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ ምግባር ችግሮችን ለይቶ እርምጃ በመውሰድ ለማጥራት እና በህዝብ ዘንድ አመኔታን ያተረፈ ተቋም ሆኖ እንዲቀጥል በግምገማዊ ስልጠናው ትኩረት መደረጉንም ጠቅሰዋል፡፡
የፖሊስ አሠራርና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ማነቆ የነበሩ ችግሮችን በማስወገድ እና በፖሊሳዊ ሥነ-ምግባርና ዲስፒሊን እንዲሁም የወንጀል መከላከልና ምርመራ ስራዎቹን በቴክኖሎጂ በማዘመን የከተማውን ሠላም በዘላቂነት ማስቀጠል እንደተቻለ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ መናገራቸውም ተመላክቷል፡፡
በታምራት ቢሻው