በመዲናዋ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ 1 ሺ ኪሎ ሜትር በላይ የሚሸፍን የመንገድ ግንባታ እና የጥገና ስራዎች ተከናውነዋል-መንገዶች ባለስልጣን

You are currently viewing በመዲናዋ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ 1 ሺ ኪሎ ሜትር በላይ የሚሸፍን የመንገድ ግንባታ እና የጥገና ስራዎች ተከናውነዋል-መንገዶች ባለስልጣን

AMN-ሚያዝያ 18/2017 ዓ.ም

ባለፉት ዘጠኝ ወራት በአጠቃላይ 1 ሺ 83 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍን ልዩ ልዩ የመንገድ ግንባታ እና የጥገና ስራዎች ማከናወኑን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ባለስልጣን መስሪያቤቱ በዘጠኝ ወራት ውስጥ 975 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ልዩ ልዩ የመንገድ ግንባታና የጥገና ስራ ለመስራት አቅዶ በድምሩ 1,083 ኪሎ ሜትር በማከናወን ከዕቅዱ በላይ መፈፀም መቻሉን ገልጿል፡፡

ከዚህም ውስጥ፤ 247 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የአስፋልት፣ የጠጠር፣ የኮብል፣ የእግረኛ መንገድ እና የፔዳል ሳይክል መተላለፊያ መንገድ ግንባታ ከማከናወኑም ባሻገር የድሬኔጅ መስመር እና የድልድይ ግንባታ ስራ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ማከናወኑን ከባለስልጣን መሥሪያቤቱ ማኅበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በሌላ በኩል የከተማዋን የመንገድ ኔትወርክ ደህንንት በማረጋገጥ የትራፊክ ፍሰቱን ለማቀላጠፍ 836 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ልዩ ልዩ የመንገድ መሠረተ ልማት ጥገና ስራዎች ተከናውነዋል ነው የተባለው ፡፡

የመንገድ የጥገና ስራዎቹ፤ የአስፋልት፣ የኮብል፣ የጠጠር፣ የእግረኛ መንገድ፣ የከርቭስቶን ግንባታና ጥገና፣ እንዲሁም የድሬኔጅ መስመር ፅዳትና ጥገና፣ ያካተቱ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review