በመዲናዋ ባለፉት 9 ወራት ከ 417 ኪሎ ሜትር በላይ የድሬኔጅ ፅዳትና የጥገና ስራዎች ተከናውነዋል

You are currently viewing በመዲናዋ ባለፉት 9 ወራት ከ 417 ኪሎ ሜትር በላይ የድሬኔጅ ፅዳትና የጥገና ስራዎች ተከናውነዋል

AMN – ሚያዚያ 24/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 9 ወራት ከ 417 ኪሎ ሜትር በላይ የድሬኔጅ ፅዳትና የጥገና ስራዎች መከናወኑን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የዘጠኝ ወራት አፈፃፀሙን ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተገምግሟል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሙህዲን ረሻድ፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 417 ኪሎ ሜትር በላይ የድሬኔጅ ፅዳትና የጥገና ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል። ዋና ዳይሬክተሩ ከባለድርሻ አካላት ጋር በተከናወኑ ተግባራት ስኬት መመዝገቡን በዚህም ከ90 በመቶ በላይ ማሳካት ተችሏል ብለዋል።

13 የሚደርሱ መንገዶች እና ድልድዮች ተጠናቀው በቅርቡ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት እንደሚደረጉ ኢንጂነር ሙህዲን ረሻድ ተናግረዋል።

በቅንጅታዊ ስራው አስተዋፅኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት እና ተቋማት ዕውቅና ተሰጥቷል።

በመሀመድኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review