በመዲናዋ እየለሙ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎች ምቹ እና ተስማሚ ከባቢን እየፈጠሩ ነው- ነዋሪዎች

You are currently viewing በመዲናዋ እየለሙ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎች ምቹ እና ተስማሚ ከባቢን እየፈጠሩ ነው- ነዋሪዎች

AMN – መጋቢት 9/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ እየለሙ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎች ምቹ እና ተስማሚ ከባቢን እየፈጠረላቸው መሆኑን የመዲናዋ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

ኤ ኤም ኤን ያነጋገራቸው የመዲናዋ ነዋሪዎች አዲስ አበባ ከተማ ከዓመታት በፊት የተጨናነቀ የትራፊክ ፍሰትን የምታስተናግድ ከመሆኗ ባሻገር እግረኞች ከመኪና ጋር የሚጋፉባት እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ይህ የመዲናዋን መልክና ገፅ ለመቀየር የተጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ የበርካታ አካባቢዎችን ገጽታ የቀየረ ከተማዋም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንድትሆን አስችሏል፡፡ በመጀመሪያው ዙር የነበሩ ክፍተቶችን በመለየትና በማሻሻልም ሁለተኛ ምዕራፍ የኮሪደር ልማት እየተከናወነ ይገኛል፡፡

የኮሪደር ልማት ስራው ሳቢ እና ማራኪ እይታን ከመፍጠር ባለፈ የበርካቶች የአኗኗር ዘይቤ እንዲለወጥም ምክንያት መሆኑን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

በመጀመሪያ ዙር የኮሪደር ልማት የትራንስፖርት ፍሰቱ እንዲሳለጥ ማድረጉን በመግለጽ ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ሲጠናቀቅ የበለጠ ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በመዲናዋ እየተገነባ ያለው የኮሪደር ልማት ስራ ለበርካቶች የስራ እድልን እንደፈጠረም የስራ እድል ተጠቃሚዎች ገልጸዋል፡፡

የተገነቡና እየተገነቡ ያሉ የልማት ስራዎችን ማህበረሰቡ በእኔነት ስሜት መጠበቅ እንዳለበትም ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

በሄለን ጀንበሬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review