ከኮልፌ ቀራኒዮ እና ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የተወጣጡ የንግዱ ማህበረሰብ ክፍል በከተማው የተገነቡ እና እየተገነቡ ያሉ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው።
የጉብኝቱ አላማ የንግዱ ማህበረሰብ የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን በተጨባጭ በመረዳት የራሳቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ለማስቻል እንደሚያግዝ ተመላክቷል።
ነጋዴዎቹ በሚዲያዎች ይሰሙት ከነበረው በቦታው ተገኝተው በተጨባጭ ማየታቸው ልዩ ስሜት እንደፈጠረባቸው ለኤ ኤም ኤን ገልጸዋል።
መንግስት እያከናወናቸው ያሉት ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች በትውልድ ግንባታ ላይ የራሳቸው በጎ ሚና አላቸው ያሉት ነጋዴዎች ይህንን መልካም ጅማሮ ለማስቀጠል የራሳቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል።
በመሀመድኑር አሊ