በጤና ተቋማት የመድሃኒት ብክነትን ለመከላከል በየተቋማቱ ያሉ መድሀኒቶችን በመለየት የቅብብሎሽ ሰንሰለት በመዘርጋት ብክነትን ከ2 በመቶ በታች ማድረስ መቻሉን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የመድሃኒትና ህክምና መሳሪያዎች አቅርቦትና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ ነፃነት ዲሮ ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የመድሃኒትና የህክምና መሳሪያዎች አቅርቦት አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በዘርፉ ባለፉት 9 ወራት የተከናወኑ ተግባራትን ገምግሟል።
ወይዘሮ ነፃነት ዲሮ በተቋማት የተበላሹ የህክምና መሳሪያዎችን በዘመቻ ጥገና ማካሄድ በመቻሉ ከ2 ሚሊየን 700 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ወጪ ማዳን መቻሉም ተገልጿል።
በሁሉም ሆስፒታሎች እና በ39 ጤና ጣቢያዎች የጥገና ማዕከላት መኖራቸዉ የሚበላሹ መሳሪያዎች በፍጥነት ተጠግነው አገልግሎት የሚሰጡበት ሁኔታ መፈጠር መቻሉን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።