በመዲናዋ የሚገኙ 40 ሆቴሎች የደረጃ ምደባ ይፋ ተደረገ

You are currently viewing በመዲናዋ የሚገኙ 40 ሆቴሎች የደረጃ ምደባ ይፋ ተደረገ

AMN-ግንቦት 21/2017 ዓ.ም

የቱሪዝም ሚኒስቴር በ2017 በጀት ዓመት መገኛቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ 92 ሆቴሎች ላይ ሲያደርግ የቆየውን የደረጃ ምደባ ስራ ውጤት ዛሬ ይፋ አድርጓል።

በዚህም ምዘና ከተደረገባቸው 92 የመዲናይቱ ሆቴሎች ውስጥ 40 የሚሆኑት ብቻ በተለያየ እርከን የኮከብ ደረጃዎችን ማግኘት እንደቻሉ ተገልጿል።

11 ሆቴሎች ባለ 5 ኮከብ፤ 9 ሆቴሎች ባለ 4 ኮከብ፤7 ሆቴሎች ባለ 3 ኮከብ፤5 ሆቴሎች ባለ 2 ኮከብ እና 2 ሆቴሎች ባለ 1 ኮከብ ሆነው መመደባቸውን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይፋ አድርጓል።

ከ40ዎቹ ሆቴሎች ውስጥ 34 የሚሆኑት ዳግም ምደባ የተደረገባቸው ሲሆኑ፥ 6 የሚሆኑት ዘርፉን የተቀላቀሉ አዳዲስ ሆቴሎች መሆናቸው ተገልጿል።

ይህ የኮከብ ምደባ የሚያገለግለው ለቀጣዮቹ 3 ዓመታት ብቻ መሆኑም ተነግሯል።

በላይሁን ፍሰሃ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review