በመዲናዋ የሚፈጸም የወንጀል ምጣኔ 43 በመቶ መቀነሱ ተገለጸ

You are currently viewing በመዲናዋ የሚፈጸም የወንጀል ምጣኔ 43 በመቶ መቀነሱ ተገለጸ

AMN – ግንቦት 14/2017 ዓ.ም

ህዝቡን የሰላሙ ባለቤት በማድረግ በተሰሩ ሥራዎች በመዲናዋ የሚፈጸም የወንጀል ምጣኔ 43 በመቶ መቀነሱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ ተናግረዋል፡፡

ኃላፊዋ በከተማዋ ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ የታጠቀ እና ከፍተኛ የመፈጸም አቅም ያለው የጸጥታ መዋቅር ለመገንባት ወጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል፡፡

በዚህም የሽብር ኃይሎችን መፈናፈኛ በማሳጣት እና የጸረ ሰላም ኃይሎችን እኩይ አላማ በማክሸፍ በከተማዋ አስተማማኝ ሰላም ማስፈን መቻሉን አስታውቀዋል፡፡

በመዲናዋ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ለ24 ሰዓታት መከናወናቸው እንዲሁም በርካታ ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ጉባዔዎች በስኬት መጠናቀቃቸው በሰላም ማስጠበቅ ሥራው የተገኙ ትሩፋቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይም ህዝቡ በመንግስት ላይ ያለው እምነት ለመሸርሸር ውዥንብር የሚነዙ እና ስልጣን በኃይል ለመያዝ የሚሰሩ አካላትን ሴራ ለመመከትበቅንጅት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ህገ ወጥ ተግባራን በመከላከል የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ይገባል ያሉት ወ/ሮ ሊዲያ ፤ ህዝብን ማዕከል በማድረግ መዲናዋን የሚመጥኑ የጸጥታ ተቋማትን የመገንባት ሥራዉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የመዲናዋን ሰላም እና ጸጥታ በማስጠበቅ ረገድ በተመዘገቡ ስኬቶች እና ባጋጠሙ ችግሮች ላይ ከጸጥታ ተቋማት ጋር ውይይት አካሂዷል።

በሔኖክ ዘነበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review