AMN – መጋቢት 10/2017
በመዲናዋ የተሰሩ የልማት ስራዎች የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እና የከተማዋን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በተጨባጭ የሚያሳዩ መሆናቸዉን የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች እና ምሁራን ገለጹ::
የዩኒቨርስቲዉ ከፍተኛ አመራሮች እና ምሁራን በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ እና ለአገልግሎት ክፍት የሆኑ ልማቶችን ጎብኝተዋል፡፡
አመራሮቹ እና ምሁራኑ የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዐከል፣ የገላን ጉራ የመኖሪያ መንደርን እና የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
በመዲናዋ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች ዜጎችን ታሳቢ ያደረጉ፣ ሀገርን በሁለንተናዊ መልኩ የሚቀይሩ እና ለአዲስ አበባም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን የሚያጎናፅፉ ናቸዉ ብለዋል፡፡
በተመስገን ይመር