በመዲናዋ የተገነቡ መሰረተ ልማቶች ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ መፍጠር የሚያስችሉ መሆናቸዉን በመዲናዋ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡
የጤና ባለሙያዎቹ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ጎበኝተዋል::
በክፍለ ከተማው ከተከናወኑ እና በባለ ሙያዎቹ ከተጎበኙ የልማት ስራዎች መካከል የገላን ጉራ መኖሪያ መንደር፣ የለነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ይገኝበታል።
መሰረተ ልማቶቹ ጽዱ እና ለጤና ተስማሚ ሆነዉ ማየታቸዉ፣ በአካልና በአዕምሮ የዳበረ እንዲሁም ከመተንፍሻ አካላት ጋር የተያያዙ በሽታዎችን ለመከላከል አጋዥ መሆናቸዉንም ጠቁመዋል::
በቴዎድሮስ ይሳ