በመዲናዋ በቀጣይ ስድስት ወራት የፕላስቲክ፣ የውሃ እና አፈር እንዲሁም የድምፅ ብክለትን ለመከላከል ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአከባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል።
የከተማ አስተዳደሩ የአከባቢ ብክለትን ለመከላከል እስካሁን ባከናወናቸው ተግበራት አበረታች ለውጦች እየተመዘገቡ መምጣታቸውን ባለሥልጣኑ ገልጿል።
ባለሥልጣኑ በበጀት ዓመቱ ስለተሠሩ ስራዎች ከተለያዩ ሲቪክ ማህበራት እና ባለድርሻ አከላት ጋር ውይይት አከሂዷል።

ንጹህና ለነዋሪዎች ምቹ አከባቢን ለመፍጠር በከተማ አስተዳደሩ እና በባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰፋፊ ስራዎች መሠራታቸውን የጠቀሱት የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዲዳ ድሪባ፣ በተለይም በአረንጓዴ ልማት ሽፋንና በወንዞች ዳርቻ ልማቶች አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።
በቀጣይ ስድስት ወራትም የበለጠ ለውጥ ለማስመዝገብ የፕላስቲክ፣ የውሃ እና አፈር እንዲሁም የድምፅ ብክለትን ለመከላከል ባለሥልጣኑ ትኩረት ሰጥቶ ይሠራል ብለዋል።
በአለሙ ኢላላ