በመዲናዋ የአደጋ ስጋት የሆኑ ቦታዎችን በመለየት 20 ሄክታር መሬት መልሶ ማልማት መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ገለጸ

You are currently viewing በመዲናዋ የአደጋ ስጋት የሆኑ ቦታዎችን በመለየት 20 ሄክታር መሬት መልሶ ማልማት መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ገለጸ

AMN – ግንቦት 18/2017 ዓ.ም

በተያዘው የክረምት ወቅት የሚደርስ አደጋን ለመቀነስ ለካባ ድንጋይ ማውጫ ተቆፍረው በተተው 25 ለአደጋ አጋላጭ የሆኑ ስፍራዎችን በጥናት በመለየት 20 ሄክታር መሬትን የማልማት ስራ እየተሰራ መሆኑም የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዲዳ ድሪባ ገልጸዋል፡፡

በመዲናዋ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ለረጅም ጊዚያት ማዕድናት ከወጡ በኋላ ሳይለሙ ተቆፋፍረው በተቀመጡ ስፍራዎች የተለያዩ ጉዳቶች ሲደርሱ እንደነበር ሃላፊው ገልጸዋል፡፡

ይህንን አደጋም ለመከላከል ከአዲስ አባባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽንና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑንም አክለዋል፡፡

በዘርፉ የሚገቡ መንግስታዊም ይሁን መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትና ግለሰቦች ቦታውን አልምቶ ለመውጣት ውል መኖሩን የሚናገሩት ዋና ስራ አስኪያጁ፣ በገቡት ውል መሰረት አልምተው የሚወጡ እንዳሉ ሁሉ ግዴታቸውን ማይወጡት ለአካበቢ ጥበቃው ስራ እንቅፋት እንደሆነባቸው ጠቁመዋል፡፡

ክረምቱን ተከትሎ የካባ ድንጋይ ማውጫ አካባቢ የመሬት መንሸራተትና መናድ ሊደርስ የሚችል አደጋን ለመከላከል በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ አካላት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አሳስቧል።

በሽታሁን መንግስቴ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review