
AMN ህዳር 23/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የ2017 ከተማ አቀፍ የ3 ወር የስራ እድል ፈጠራ ንቅናቄ uአስተሳሰብ ቀረጻ እና የሌማት ቱሩፋት እቅድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የቢሮ አመራሮች ጨምሮ የሁሉም ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፖርቲ ወጣቶች ሊግ አመራሮች፣ የወጣት ማህበር አመራሮች፣ የማዕከል የወጣት ዘርፍ ባለሙያዎች፣ የወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና የዘርፉ ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን፤ ያሉ ጸጋዎች በመጠቀም Kስራ ፈላጊ ወጣቶች ቋሚ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የንቅናቄ እና የማይንድ ሴት ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ አስታውሰው በቀጣይ ሦስት ወራት የሚከናወነው ወጣቶችን የመለየት የመመዝገብና ግንዛቤ የመፍጠር ስራ በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲመራ አሳስበዋል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ ከ150ሺ በላይ ወጣቶች በቋሚ የስራ ዕድል ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የታቀደው እቅድ ተግባራዊ እንዲሆን ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን ያወሱት ሃላፊው& ውጤታማ የሆነው ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ስራ ወጣቱ ጠባቂ እንዳይሆን አስችሎታል ብለዋል፡፡

የወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቀጣይ ሦስት ወራት በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ገለጻ ያደረጉት የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መክብብ ወልደሃና ከብሎክ እስከ ማዕከል በሚሰሩ ስራዎች የአገሪቱን ለውጥ መነሻ በማደረግ ባሉ አስቻይ ሁኔታዎች ጨምሮ በኢኮኖሚ ሪፎርም፣ ዲጂታል ሪፎርም እና አገር በቀል ፈጠራዎች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽሕፈት ቤት ፕሬዚዳንት መለስ አባተ በበኩላቸው፤ ወጣቱን በፖለቲካዊ ፣ በኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ ጉዳዮች ተጠቃሚ ለማድረግ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸው፤ ከተማ አስተዳደሩ ያቀደውን እቅድ ለማስካት በአስተሳሰብ ቀረጻ እና ንቅናቄ ላይ በቅንጅት እንዲሰራ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
ቢሮ ኃላፊው በሰጡት የስራ አቅጣጫ፣ የስራ እድል ፈጠራና የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ እቅዱን ከግብ ለማድረስ ወጣቶችን በተደራጀ መንገድ መመዝገብ፣ ግንዛቤ በመፍጠር ወደ ስልጠና በማስገባትና መስሪያ ቦታ እና ብድር ማመቻቸት በትኩረት እንዲሰራ ማሳሰባቸውን Ÿቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡