በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው

You are currently viewing በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው

AMN – የካቲት 17/2017 ዓ.ም

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ሕዝባዊ ውይይት መካሄድ ጀምሯል፡፡

ውይይቱ በብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ የተቀመጡ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች እንዲሁም በልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው፡፡

“ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው የፓርቲው ጉባኤ መነሻ ሀሳብ መሰረት፣ “መፍጠንና መፍጠር ለጉባኤ ውሳኔዎች ስኬት” በሚል መሪ ሀሳብ ነው ሕዝባዊ ውይይቱ እየተካሄደ የሚገኘው።

የብልፅግና ፓርቲ ሰራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና በሚኒስትር ማዕረግ የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ እና በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉነሽ ደሴ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ የሚገኘውን ሀገር አቀፍ የሕዝብ ውይይቱን በመምራት ላይ ናቸው፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች እየተሳተፉ እንደሚገኙ ከማዕከላዊ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review