በማይናማር በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ እስካሁን ድረስ የሟቾቹ ቁጥር ከ2000 በላይ መድረሱ ተገልጿል።
በዚህ አደጋ፣ እስካሁን 2056 ሰዎች እንደሞቱ የተረጋገጠ ሲሆን፣ ህንፃ ተደርምሶባቸው ለሦስት ቀናት መውጫ አጥተው የነበሩ ሰዎችም የነፍስ አድን ቡድን ባደረገው ርብርብ የተወሰኑ ሰዎችን በህይወት ማውጣት መቻሉ ተረጋግጧል።
ማይናማር ለምዕተ አመት በጦርነት ስትታመስ የኖረች ሀገር ስትሆን አርብ ዕለት የተከሰተውና በሬክተር እስኬል 7 ነጥብ 7 የተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀ ባደረሰባት ከባድ ውድመት ከ2000 በላይ የሚሆኑ ዜጎቿ መሞታቸው ተረጋግጠዋል።
አደጋው ከአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን በላይ ዜጎቹን ያፈናቀለ ሲሆን ጥንታዊ እና ታሪካዊ ህንፃዎቿንም ማውደሙ ተዘግቧል።
አርብ ዕለት በተከሰተው እና ከፍተኛ ቁጥር ያስመዘገበው ገዳዩ የተፈጥሮ አደጋ የመገናኛ አውታሮችን፣ የጤና መሠረተ ልማቶችን እና ሚሊዮኖችን አፈናቅሎ አልፏል።
በዚህም 2056 ሰዎች መሞታቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከ3 ሺህ 900 በላይ የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸውን፣ ሦስት መቶ ሰዎች ደግሞ ደብዛቸው መጥፋቱን ከሲኤን ኤን የተገኘው መረጃ ያስረዳል።
በወርቅነህ አቢዬ