በማይናማር በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ1 ሺህ 700 ማለፉ ተገለጸ

You are currently viewing በማይናማር በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ1 ሺህ 700 ማለፉ ተገለጸ

AMN – መጋቢት 22/2017

በማይናማር በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ እስካሁን ከ1 ሺህ 700 በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገልጿል፡፡

የማይናማር መንግስት የዜጎችን ህልፈት ተከትሎ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ብሔራዊ የሀዘን ቀን አውጇል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) በበኩሉ፣ ለጉዳቱ የሚሆን 8 ሚሊየን ዶላር አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ገልጿል፡፡

በማይናማር የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ፣ ንዝረቱ ጎረቤት ሀገር ታይላንድ ድረስ የተሰማ ሲሆን፣ በዛም ባስከተለው የህንፃዎች መደርመስ አደጋ የ19 ሰዎች ሕወይት ማለፉ ተመላክቷል፡፡

በዛሬው እለትም በሺዎች የሚቆጠሩ የባንኮክ ከተማ ነዋሪዎች ጉዳት ከደረሰባቸው ህንፃዎች እየሸሹ መሆናቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡

በማሬ ቃጦ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review