በሪፎርሙ በተከናወኑ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ኢትዮጵያን በዓለም ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ካስመዘገቡ ሀገራት ተርታ ማሰለፍ ተችሏል – ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር)

You are currently viewing በሪፎርሙ በተከናወኑ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ኢትዮጵያን በዓለም ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ካስመዘገቡ ሀገራት ተርታ ማሰለፍ ተችሏል – ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር)

AMN-ታህሣሥ 16/2017 ዓ.ም

በሪፎርሙ በተከናወኑ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ኢትዮጵያን በዓለም ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ካስመዘገቡ ሀገራት ተርታ ማሰለፍ መቻሉን የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር) ገለጹ።

በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በአማካይ 7 ነጥብ 2 በመቶ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት በማስመዝገብ ከምስራቅ አፍሪካ ትልቁን ምጣኔ ሃብት የገነባች ሀገር መሆኗንም ጠቅሰዋል።

በሌሎች የኢኮኖሚ አመላካች ዘርፎችም አመርቂ ውጤቶች የተመዘገቡ መሆኑን ጠቅሰው ከዚህ ቀደም የነበሩት የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባትን በዘላቂነት የመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

በተለይም በማክሮ ኢኮኖሚ ትግበራና በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ዘርፈ ብዙ ስኬቶች መመዝገባቸውን አንስተዋል።

በተለይም በግብርና፣ በማዕድን፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በቱሪዝም፣ በዲጂታል ልማትና ሌሎች ዘርፎችም ከፍተኛ እድገትና ስኬት እየተገኘ መሆኑን ተናግረዋል።

በንግድና ኢንቨስትመንት መስክም የውጭና የሀገር ውስጥ ባለሃብቶችን የሚያበረታቱ ስራዎች ተግባራዊ መደረጋቸውንም አንስተዋል።

በገንዘብ ፖሊሲም ከዚህ በፊት የነበረውን ጉድለት መሙላት ያስቻሉ የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውን ሚኒስትሯ ጠቅሰዋል።

የገቢ መጠንን በማሳደግ ረገድም ከፍተኛ እድገትና መሻሻል ማሳየት የተቻለበት አጋጣሚ መፈጠሩን ነው የተናገሩት።

የመንግስት ልማት ድርጅቶች ትርፋማነትም እያደገ መምጣቱን ጠቅሰው ኢትዮ-ቴሌኮም ብቻ ባለፈው ዓመት 27 ቢሊዮን ብር ታክስ መክፈሉን ማንሳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በመስኖ ልማት ስራ በተለይም በበጋ መስኖ ልማት ባለፈው ዓመት ብቻ 230 ሚሊዮን ኩንታል የስንዴ ምርት መገኘቱን ነው የጠቀሱት።

በመሰረተ ልማት ግንባታ ባለፉት ስድስት ዓመታት 27 ሺህ ኪሎ ሜትር አዲስ የመንገድ ስራ መከናወኑን ጠቁመው በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review