
AMN- ግንቦት 13/2017 ዓ.ም
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ዋሽንግተን በዩክሬን እና ሩሲያ መካከል ሩሲያ የምትወስደውን የሰላም እርምጃ እየጠበቀች ነው ያሉ ሲሆን፣ ለድርድር ልባዊ ፍላጎት ካላሳየች አዲስ ማዕቀብ ሊጣልባት እንደሚችል ጠቁመዋል።
ሩቢዮ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አካሄድ ይህን መሰል እርምጃዎችን ለማስወገድ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተው፣ ሩሲያን በእገዳ ማስፈራራት ንግግራቸውን እንዲያቆሙ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ፕሬዚዳንቱ ያምናሉ ሲሉ ተናግረዋል።
አርብ ዕለት በቱርክዬ ዋና ከተማ ኢስታንቡል በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል የሰላም ድርድር የተካሄደ ሲሆን፣ ሁለቱም ወገኖች እያንዳንዳቸው 1 ሺህ የጦር እስረኞችን ለመለዋወጥ እና የተኩስ አቁም ድርድሩን ለመቀጠል መስማማታቸውን አናዶሉ በዘገባው አስታውሷል።
በሊያት ካሳሁን