
AMN ህዳር 16/2017 ዓ .ም
በሰላም እና ደህንነት ላይ የሚመክረው አህጉር አቀፍ ጉባኤ “የበለፀገችና ሰላማዊ አፍሪካን እንገንባ” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በመድረኩ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለም፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሐፊ እና በኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታ አስተባባሪ ዶክተር ራሚዝ አላክባሮቭ፣ የአፍሪካ ሕብረት የፖለቲካ ፣ የሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዴዎዬ፣ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ተቋማት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ይህ አህጉር አቀፍ ጉባኤ ለሁለት ቀናት እንደሚቆይም ተመላክቷል፡፡
በተመስገን ይመር