በሰው ተኮር ስራዎቻችን ማህበራዊ ፍትህን ለማንገስ እየሰራን ነው-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing በሰው ተኮር ስራዎቻችን ማህበራዊ ፍትህን ለማንገስ እየሰራን ነው-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN – የካቲት 11/2017 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተማ አስተዳደሩ በበጎነት የመኖሪያ መንደር ለአቅመ ደካሞች እና የልማት ተነሺዎች ያስገነባቸውን 192 የመኖሪያ ቤቶችን የያዙ ሁለት ባለ 9 ወለል ህንጻዎች ለነዋሪዎች አስተላልፈዋል፡፡

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፣ “በሰው ተኮር ስራዎቻችን ማህበራዊ ፍትህን ለማንገስ እየሰራን ባለነው ስራ በበጎነት የመኖሪያ መንደር ለመኖር ምቹ የሆኑ ሰባት ህንጻዎችን ገንብተን ለኑሮ ምቹ ካልሆኑ አካባቢዎች ለተነሱ የከተማችን ነዋሪዎች አስተላልፈናል” ብለዋል፡፡

በበጎነት የመኖሪያ መንደር የመኖሪያ ቤት ብቻ ሳይሆን የህጻናት መጫወቻ፣ የእንጀራ መጋገሪያ ፋብሪካ፣ የጸጉር እና የልብስ ስፌት የስራ እድሎች የተካተቱበት ፣ የዜግነት ክብርን የሚመጥን ፣ንፁህ እና ውብ አካባቢ መሆኑን አንስተዋል፡፡

“ከተማችን እንደ ስሟ ውብ፣ አበባ እየሆነች ያለችው የነዋሪዎቿን ኑሮና አኗኗር በማሻሻል ጭምር ነው” ያሉት ከንቲባ አዳነች የዜጎችን ሁለተናዊ ህይወት የመቀየር ስራ በመንግስት በጀት ብቻ እንደማይሳካ ገብቶን “መስጠት አያጎድልም “በማለት በርካታ ልበ ቀና ባለሀብቶችን በማስተባበር በመስራት የበርካቶችን ህይወት መቀየር ችለናል ነው ያሉት::

ለዚህም የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አመራሮች እና ሰራተኞችን በነዋሪዎች እና በራሳቸው ስም አመስግነዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review