በስልጤ ዞን ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ እና ዞን አቀፍ የኢንቨስትመንት ፎረም በወራቤ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
በፎረሙ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ብልካን ጨምሮ ሌሎች የዞን፣የወረዳና የከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና ባለሀብቶች ተሳትፈውበታል።
በዞኑ አጠቃላይ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች፥ እምቅ የኢንቨስትመንት አቅሞች እና በዘርፉ በሚታዩ ማነቆዎችና የትኩረት መስኮች ላይ ከባለሀብቱና ከሌሎችም ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር እንደሚካሄድ ከዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል፡፡