AMN – ኅዳር 16/2017 ዓ.ም
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን 5 ወረዳወች ውስጥ በህቡዕ እየተንቀሳቀሰ ህብረተሰቡን ሰላም ሲነሳ የነበረው የሽብር ቡድን እና ተላላኪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል ክፍለጦር አስታውቋል።
የሽብር ቡድኑና ጀሌዎቹ በሌሊትና በአሳቻ ሰአት እየተንቀሳቀሱ ህዝብን ሲዘርፉ ፣ሲያፍኑ ፣ ሲገድሉና ሴቶቹን ሲደፍሩ እንደነበር የክፍለጦሩ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ፍቃዱ ጥላሁን ተናግረዋል።
በጠላት ድርጊት የተበሳጨው የአካባቢው ማህበረሰብ ለክፍለጦሩ ባደረሰው ጥቆማ መሠረት በኖኖ፣ በበቾ፣ በቶሌ፣ በአመያና፣ በቀርሳ ማሌማ ወረዳዎች ባደረገው ስምሪት 14 የጠላት ሃይል ሲደመሰስ የቀጠናው የጠላት አመራር የቅርብ አጃቢ ጃል ቢልሌን ጨምሮ 8 የሽብር ቡድኑ አባላት የተማረኩ ሲሆን ለጠላት ሎጀስቲካዊ ግልጋሎት ሲሰጡ የነበሩ 10 ግለሰቦች፣አንድ የመረጃ አባል እና 3 ምልምል በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በተወሰደው እርምጃ ጠላት ለጥፋት አላማ ሲጠቀምበት የነበረ 21 ክላሺንኮቭ መሳሪያ ከ552 ጥይት ፣ 1መትረየስ ከ135 ጥይት ፣ 6 የእጅ ቦምብ ፣ 2 ሽጉጥ ፣ 46 የክላሽ መጋዘን፣ 12 የወገብ ትጥቆች እና 5 ሞተር ሳይክሎች መማረካቸውን ኮሎኔል ፍቃዱ ጥላሁን ገልፀዋል።
በተመሳሳይ የሸኔ ታጣቂዎች በምዕራብ ሸዋ ዞን በአቡና ግንደበረት ወረዳ ተሰማርቶ ለሚገኘው የምዕራብ ዕዝ ገብርዬ ክፍለጦር እጅ ሰጥተዋል።
ሠራዊቱ በወረዳው ውስጥ ሲንቀሳቀስ በነበረው አሸባሪ ኦነግ ሸኔ ላይ እየወሰደ የሚገኘውን እርምጃ ተከትሎ የቡድኑ ታጣቂዎች ለሽብር ስራቸው ሲጠቀሙበት ከነበረው ቁሳቁስና የጦር መሳሪያ ጋር ለክፍለጦር ሠራዊት እጅ እየሰጡ መሆኑን የክፍለጦሩ ዋና አዛዦ ኮሎኔል ተካ ተፈራ ገልፀዋል።
ሠራዊቱ በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን በማስገንዘብ የሠራዊቱን ጠንካራ ምት መቋቋም ያቃታቸው እና የቡድኑን እኩይ ሴራ የተገነዘቡ ታጣቂዎችም ለሽብር ስራቸው ማስፈፀሚያ የሚጠቀሙበትን ሶላር ከነ ባትሪው ጨምሮ የጦር መሳሪያዎችንና ትጥቆችን በመያዝ እጅ መስጠታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታ