በሸገር ከተማ 135 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የኮሪደር ልማት እየተሰራ ነው -ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር)

You are currently viewing በሸገር ከተማ 135 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የኮሪደር ልማት እየተሰራ ነው -ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር)

AMN – ታኅሣሥ 23/2017 ዓ.ም

በሸገር ከተማ በመጀመሪያ ዙር የኮሪደር ልማት 135 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የተቀናጀ የኮሪደር የመሰረተ ልማት ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ተናገሩ።

በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመረው የኮሪደር ልማት በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞችም በመስፋት ላይ ነው።

የከተማዋ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) በመጀመሪያው ዙር 135 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የኮሪደር ልማት በሸገር ከተማ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

የኮሪደር ልማቱ ከተማዋን የሚያዘምኑ እና ለረጅም ዓመታት የሚያገለግሉ የተቀናጀ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን ያካተተ ነው ብለዋል።

የውሃ፣ የመብራት፣ የቴሌኮም እንዲሁም የተሽከርካሪ፣ የእግረኛ፣ የብስክሌት፣ የተሽከርካሪ ማቆሚያ፣ የህዝብ መዝናኛና ሌሎች ወሳኝ መሰረተ ልማቶች የሚገነቡበት እንደሆነም ጠቁመዋል።

በከተማዋ የሚያልፉ ዋና ዋና መንገዶች በመኖራቸው ከፌዴራል ተቋማት ጋር በትብብር እየተሰራ እንደሚገኝም አንስተዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ክፍለ ከተሞች ያላቸውን ጸጋ መሰረት በማድረግ የተለየ አደረጃጀት እንዲኖራቸው መደረጉን ነው ያብራሩት።

በዚህም መሰረት ኮዬ የፋይናንስ ማዕከል፣ ገላን የኢንዱስትሪ ማዕከል፣ እንዶዴ የሎጂስቲክስ ማዕከል፣ ሰበታ የወጪና ገቢ ምርቶች ማቀነባበሪያ ዞን፣ ሱሉልታ እና መነአቢቹ የግሪን ቤልት ዞን ይሆናሉ ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review