በቀለም ብቻ ሳይሆን በሚዳሰሱ የፈጠራ ስራዎች የታነፀ ትውልድ የመገንባት ስራዎቻችን ተጨባጭ ፍሬዎች እያፈሩ ይገኛሉ-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing በቀለም ብቻ ሳይሆን በሚዳሰሱ የፈጠራ ስራዎች የታነፀ ትውልድ የመገንባት ስራዎቻችን ተጨባጭ ፍሬዎች እያፈሩ ይገኛሉ-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN – ሚያዝያ 16/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ “በፈጠራ ስራ የተካነ ትጉ ትውልድ ለሀገር ብልፅግና” በሚል መሪ ሀሳብ የአዲስ አበባ ተማሪዎች እና መምህራን የሳይንስና ፈጠራ አውደ ርዕይ በይፋ ከፍተዋል።

ከንቲባዋ መርሐግብሩን አስመልክተው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ በመዲናዋ በልዩ ትኩረት እየተከናወኑ ካሉ የለውጥ ማሳያዎች መካከል አንዱ የሆነው የትምህርት ስርዓቱን ስብራቶች በመጠገን በቀለም ብቻ ሳይሆን በሚዳሰሱ የፈጠራ ስራዎች የታነፀ ትውልድ የመገንባት ስራዎች ተጨባጭ ፍሬዎች እያፈሩ ይገኛሉ ብለዋል።

መምህራን ለተማሪዎች የፈጠራ ስራዎች መሰረት መሆናቸውን የገለጹ ሲሆኑ፣ ተማሪዎች ደግሞ የሀገር ለውጥ መሰረት ናቸዉ ብለዋል።

በዚህ ጥረት ላይ የቤተሰብ እና መንግሥት ሚና ከታከለበት በአጭር ጊዜ ውስጥ በሁሉም የለውጥ መስኮች የጠነከረችና የፀናች ሀገር መገንባት እንደሚቻል ጠቁመዋል።

ዛሬ በይፋ የተከፈተው የሳይንስ እና ፈጠራ አውደ ርዕይ፣ በተማሪዎች መካከል ውጤታማ ውድድርን ከማስፍን ጎን ለጎን በከተማዋ እየተከናወነ ላለው መጠነ ሰፊ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጦችም አይነተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑን አንስተዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ በትምህርት ዘርፉ ላይ የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review