AMN-ጥር 12/2017 ዓ.ም
የእስራኤል እና ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነትን ተከትሎ በቀይ ባህር በንግድ መርከቦች ላይ ይደርስ የነበረው ጥቃት መቀነሱ ተገልጿል፡፡
የተኩስ አቁሙ ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ የየመን ሁቲ አማጽያን በቀይ ባህር ከእስራኤል ጋር ግንኙነት አላቸው በተባሉ የንግድ መርከቦች ላይ ይፈፅሙት የነበረውን ጥቃት ጋብ ማድረጋቸው ተገልጿል።
በሁቲ እና በላኪዎች መካከል ቅንጅት ለመፍጠር የሚሰራው የሰብዓዊ ተልዕኮ ማስተባበሪያ ማዕከል በትናንትናው ዕለት ለላኪዎች ባሰራጨው ኢሜይል፣ ቡድኑ ቀደም ሲል ዒላማ ባደርጋቸው መርከቦች ላይ እየሰነዘረ የሚገኘውን ጥቃት ማቆሙን አስታውቋል።
እስራኤልን በጠላትነት ፈርጆ የሚንቀሳቀሰው ዓማፂ ቡድን፣ በጋዛ ጦርነት ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ በዓለምአቀፍ መርከቦች ላይ ከ100 የሚልቁ የድሮን እና የሚሳኤል ጥቃት መሰንዘሩን ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል።
Like
Comment
Copy
Share