በቀጠናው የሚገኘው ሠራዊት በፅንፈኛው ቡድን ላይ እርምጃ ወስዷል

AMN ጥር 9/2017 ዓ.ም

የምስራቅ ዕዝ ኮሮች በተሰማሩባቸው የጎጃም ዞኖች ከ100 በላይ የፅንፈኛውን ቡድን በመደምሰስ 07 በመማረክ በርካታ ትጥቆችንና ሎጂስቲክሳዊ ማቴሪያሎችን በቁጥጥር ስር አውለዋል፡፡

የምስራቅ ዕዝ ኮር በአዊ ዞን ያዩ ጓጉሳ ወረዳ ኡሁድት አካባቢ ባደረጉት ስምሪትና ኦፕሬሽን 27 ክለሽ በመማረክ አካባቢውን ከፅንፈኛው ነፃ የማድረግ ግዳጅ ተወጥተዋል።

በምስራቅ ጎጃም ዞን በአማኑኤልና ደብረ ኤሊያስ ወረዳዎችና አካባቢ የሚገኙት የሠራዊት አባላት ባደረጉት ስምሪት በርካታ የፅንፈኛውን አባላት በመደምሰስ ፅንፈኛው ሲገለገልበት የነበረ ስናይፐር፣ በርካታ ክላሽ፣ ሬድዮ፣ ሽጉጥና ኋላ ቀር መሳሪያዎች እንዲሁም 58 ኩንታል እህል በቁጥጥር ሥር አውለዋል።

በሌላ በኩል የምዕራብ ዕዝ አንድ ኮር በምስራቅ ጎጃም ዞን ገዳ እየሱስ፣ ሰኞ ገበያ፣ የቁራ፣ ራስ አማና ዮዲት ቀበሌ አካባቢ ስምሪቶችን በማድረግ በፅንፈኛው ላይ የተቀናጀ እርምጃ በመውስድ በርካታ መሳሪያዎችን በመማረክ በፅንፈኛው ላይ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንዲደርስ ተደርጓል፡፡

ከፅንፈኛ ቡድን የተማረኩ መሳሪያዎችን በየአካባቢው ተሰማርቶ ግዳጁን እየተወጣ ለሚገኘው የፀጥታ ሃይል ማስታጠቅ ተችሏል።

የክልሉን ሰላም መስፈን የማይሹ የፅንፈኛው ተላላኪዎች ህገ-ወጥ ተግባራቸው በሰራዊታችን ክትትል እየመከነ መሆኑን እና የየአካባቢው ማህበረሰብ ከፀጥታ አባላት ጋር የተቀናጀ ስራ በመሰራት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ የትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

All reactions:

395You, Abayo Gebre Silasie, Dhugaan Dorrobde and 392 others

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review