በቀጣይ ዘጠና ቀናት ለዘጠና ሺ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ

You are currently viewing በቀጣይ ዘጠና ቀናት ለዘጠና ሺ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ

AMN – ሰኔ 11/2017 ዓ.ም

በቀጣይ ዘጠና ቀናት ለዘጠና ሺ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው በነዚህ የዘጠና ቀናት ንቅናቄው የስራ እድል ፈጠራ የከተማ ግብርና የተረጂነት እሳቤን መቀልበስ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ስለመሆናቸውም የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጥራቱ በየነ ለ ኤ ኤ ምኤን ተናግረዋል።

ያሉንን ፅጋዎች ዜጎች ባግባቡ እንዲጠቀሙና ከራሳቸውም አልፎ ሀገርንም የሚያሻግር ተግባር እንዲያከናውኑ ለማስቻል ቢሮው ወጣቱን በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በማሰልጠን እና የስራ እድል በመፍጠር ተጠቃሚ ለማድረግም በትኩረት እየሰራ ስለመሆኑም አንስተዋል፡፡

በተለይ መጪው የክረምት ጊዚያት ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ የሌማት ቱሩፍትና የከተማ ግብርና ተቀዳሚው ተግባር መሆኑን ያነሱት አቶ ጥራቱ በየነ ይህንንም በከፍተኛ የህዝብ ንቅናቄ የሚተገበሩ ስለመሆናቸውም ጠቁመው ነዋሪው በዚህ ንቅናቄ ተሳታፊ እንዲሆንም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ባለፉት አስራ አንድ ወራት ብቻ በተከናወኑ ተግባራት ከ341 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ እድል ስለመፈጠሩም ተመላክቷል፡፡

በራሄል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review