በበጀት ዓመቱ በመዲናዋ አንድም ቦታ ላይ የመሬት ወረራ አለመደረጉን የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ገለጸ

You are currently viewing በበጀት ዓመቱ በመዲናዋ አንድም ቦታ ላይ የመሬት ወረራ አለመደረጉን የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ገለጸ

AMN – ሰኔ 6/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማን ከመሬት ወረራ ፅዱ ለማድረግ በትኩረት በተከናወነው ተግባር፣ በበጀት ዓመቱ 11 ወራት የመሬት ወራራን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት መቻሉን የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ገልጿል፡፡

የባለስልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ ለኤኤምኤን FM 96.3 ሬዲዮ እንደተናገሩት፣ ከአሁን ቀደም ለከተማዋ ፈተና ከነበሩ ችግሮች መካከል የመሬት ወረራ አንዱ ነው፡፡

ችግሩን ለመቅረፍ ባለስልጣኑ ከነዋሪው ጋር በተቀናጀ መልክ መሥራት በመቻሉ ከመሬት ወረራ ጋር ተያይዞ አንድም ችግር ያልታየበት ዓመት መሆኑን አስታውቀዋል።

ከተማዋ ወደ ዘመናዊነት ለምታደርገው ጉዞ መሬትን በአግባቡ መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን ያነሱት ምክትል ሥራ አስኪያጁ ነዋሪው ማህበረሰብም ይህን ተገንዝቦ ተባባሪ እየሆነ በመምጣቱ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል፡፡

በሲሳይ ንብረቱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review