በባህር ዳር ከተማ ለፅንፈኛው ሊተላለፍ የተዘጋጀ የጦር መሳሪያ ተያዘ

You are currently viewing በባህር ዳር ከተማ ለፅንፈኛው ሊተላለፍ የተዘጋጀ የጦር መሳሪያ ተያዘ

AMN-ኅዳር 19/2017 ዓ.ም

በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ ለፅንፈኛው ቡድን እኩይ አላማ ማስፈፀሚያ የተዘጋጀ የጦር መሳሪያ በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ መያዝ መቻሉን የኮማንዶ ሬጅመንት ዋና አዛዥ ሻለቃ ታጠቅ ገብረመድህን አስታወቁ።

እነዚህ የጦር መሳሪያዎች ለአካባቢው ሰላምና መረጋጋት ትልቅ እንቅፋት ይሆኑ የነበረ ሲሆን ሠራዊቱ በደረገው ክትትል መያዛቸው ለህዝብ ደህንነትና ሰላም ጉልህ ሚና አለው ብለዋል፡፡

ከፍተኛ መኮንኑ በተደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ ኤ ኬም ጠብመንጃ ፤ ኋላ ቀር ጠብ መንጃዎች ፤ልዩ ልዩ ሽጉጦች፤ የኤ ኬም ጠመንጃ ተተኳሽ 419፤ የልዩ ልዩ ሽጉጥ ተተኳሽ 136፤ 01 ሳንጃ እና ልዩ ልዩ የሚሊተሪ አልባሳቶች መገኘታቸውን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ በሰሜን ወሎ ዞን ፅንፈኛውን ቡድን ተቀላቅለው በሽብርተኝነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቡድኑ አባላት በአካባቢው ለሚገኘው የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ክፍለ ጦር እጅ ሰጥተዋል።

መቶ አለቃ ተሾመ ሰለሞን ቡድኑ እያራመደ ያለው የፅንፈኝነት ተግባር እቆምለታለሁ የሚለውን ህዝብ ኑሮ እና ህይወት ከዕለት ዕለት እያቃወሰና ለከፋ ችግር እየዳረገ እንደሚገኝ ጠቅሰው አባላቱም ይህን በመረዳት ለመከላከያ ሠራዊት እጅ መሥጠታቸውን መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review