AMN – ጥር 13/2017 ዓ.ም
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ የተሰማሩ የኢትዮጵያ ፖሊስ መኮንኖች ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጀግኖች ማዕከል 6 መቶ 34 ሺህ 5 መቶ ብር ድጋፍ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፣ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጀግኖች ማዕከል የተደረገው ድጋፍ ለሌሎችም በትምህርትነት የሚወሰድ መሆኑን ተናግረው ለተደረገው ድጋፍ በማኔጅመንቱና በፖሊስ ሠራዊቱ ስም ምስጋና ማቅረባቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።