በተደረገልን ድጋፍ ብቸኝነት ሳይሰማን በዓሉን በደስታ እያከበርን ነው፡- አቅመ ደካሞች

You are currently viewing በተደረገልን ድጋፍ ብቸኝነት ሳይሰማን በዓሉን በደስታ እያከበርን ነው፡- አቅመ ደካሞች

AMN-ሚያዝያ 12/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር የማህበራዊ ትረስት ፈንድ ጽ/ቤት የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከከተማዋ የመሬት ይዞታ፤ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር በቂርቆስ ክፍለከተማ የተስፋ ብርሀን ምገባ ማዕከል ለአቅመ ደካሞች ማዕድ በማጋራት አሳልፏል፡፡

ማዕድ ማጋራቱ ለሀገር ውለታ ለሰሩ እና አሁን ላይ ጠዋሪ ላጡ ወገኖች እንዲሁም በተለያየ ችግር ምክንያት አቅም ላጠራቸው ወጣቶች የተደረገ መረሀ ግብር እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በአሉን በጋራ ማሳላፋቸው እንዳስደሰታቸው እና የወገንን ፍቅር ያያነበት ነው ሲሉ ማዕድ የተጋሩ አቅመ ደካሞች ተናግረዋል።

በሩዝሊን መሃመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review