በቴህራን ቁልፍ ወታደራዊ ሰው መገደላቸውን ተከትሎ፣ ኢራን በእስራኤል ላይ አዲስ የአየር ጥቃት ሰነዘረች

You are currently viewing በቴህራን ቁልፍ ወታደራዊ ሰው መገደላቸውን ተከትሎ፣ ኢራን በእስራኤል ላይ አዲስ የአየር ጥቃት ሰነዘረች

AMN- ሰኔ 9/2017 ዓ.ም

እስራኤል የቴህራንን ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር መግደሏን ተከትሎ፣ ኢራን ሌሊቱን አዲስ የአየር ጥቃት በእስራኤል ላይ መሰንዘሯ ተገልጿል።

የኢራን እና የእሥራኤል ግጭት ቀጥሎ፣ የአየር እና የሚሳኤል ጥቃት በመባባሱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ውጥረቱ አይሏል።

በትላንትናው እለት እስራኤል በፈጸመችው የአየር ጥቃት፣ የኢራን ጦር ኃይል የስለላ ክፍል ዋና አዛዥ መገደላቸው የተነገረ ሲሆን፣ ይህንንም ተከትሎ ኢራን በወሰደችው የአጸፋ እርምጃ 10 እስራኤላውያን መገደላቸው ተዘግቧል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ሁለቱም ወገኖች የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ይሁን እንጂ ጥቃት እየደረሰብኝ ባለበት ሁኔታ ውስጥ ምንም አይነት የተኩስ አቁም ስምምነት አላደርግም ስትል ኢራን ማስታወቋ ተሰምቷል።

እስራኤል ከዓርብ ጀምሮ በሰነዘረችው የአየር ጥቃት ከ224 በላይ ኢራናውያን መገደላቸውን የኢራን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ኢራን በበኩሏ ከዓርብ ጀምሮ በወሰደችው የአጸፋ እርምጃ 19 እስራኤላውያን መገደላቸውን ባለስልጣናት መናገራቸው ተገልጿል፡፡

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ፣ ጉዳዩ ጦርነቱ እንዳይባባስ ማድረግ ሳይሆን፣ ኢራንን ኒዉክሌር ከመታጠቅ ማስቆም ነው ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review