ነባሩ ፓስፖርት የአገልግሎት ጊዜው እስኪያበቃ ጥቅም ላይ መዋሉን ይቀጥላል፣
የዕድሳት ጊዜው ሲደርስ በኢ-ፓስፖርት ይተካል፣
እድሜአቸው ከ25 አመት በላይ ለሆኑ የአገልግሎት ጊዜው 10 አመት ነው፣
14 አዳዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈት አገልግሎቱን ለመስጠት ዝግጅት ተጠናቋል፣
ከአንድ ነጥብ 5 ሚልየን በላይ ኢ-ፓስፖርት ታትሞ ተዘጋጅቷል፣
ከፓስፖርት በተጨማሪ ከ10 በላይ የጉዞ ሰነዶችን እንዲዘምኑ ማድረግ ተችሏል፣
አዲሱ የኢ-ፓስፖርት በነበረው ዋጋ ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ይሆናል።
ተቋሙ ሪፎርም ማድረግ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የጉዞ ሰነዶችን ዘመናዊ ለማድረግ እየሰራ ቆይቷል፣
ሀገራችን ለፓስፖርት ህትመት የምታወጣውን የውጭ ምንዛሬ በማስቀረት የሚኖረው ፋይዳ ጉልህ ነው፣
ከዚህ በፊት አገልግሎት እየተሰጠ የቆየው 20 ዓመት ባለፈው ቴክኖሎጂ ነው፣
ይህንን ቴክኖሎጂ በሀገር ውስጥ መገንባት መቻሉ ትልቅ ድል ነው፣
አዲሱ ቴክኖሎጂ ግን ደንበኞች ባሉበት ፓስፖርታቸውን በፍጥነት ማግኘት እንዲችሉ ያደርጋል፣
ከዚህ በፊት የሚያጋጥሙ የደህንነት ችግሮችን ሙሉ በሙሉ ይቀርፋል፣
አዲሱ ኢ-ፓስፖርት እስከአሁን ኢትዮጵያ ካላት ፓስፖርት በአይነቱና በደረጃው እጅግ ከፍ ያለ እና አለም የደረሰበት የመጨረሻው ቴክኖሎጅን በመጠቀም የተዘጋጀ የጉዞ ሰነድ ነው።
ምንጭ-የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት