በናይጄሪያ በደረሰ የጎርፍ አደጋ ከ700 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ

You are currently viewing በናይጄሪያ በደረሰ የጎርፍ አደጋ ከ700 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ

AMN – ግንቦት 25/2017 ዓ.ም

ሃሙስ ዕለት በናይጄሪያ ሞክዋ ከተማ በደረሰው አውዳሚ ጎርፍ ሳቢያ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ200 በላይ መድረሱን የአካባቢው ባለስልጣናት ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በማዕከላዊ ኒጀር ግዛት አደጋው መከሰቱን ተከትሎ 500 ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም ተብሏል።

የአካባቢው ባለሥልጣን የሆኑት ሙሳ ኪምቦኩ እንደገለጹት፤ በአካባቢው ሰዎችን በህይወት ማግኘት አዳጋች በመሆኑ የነፍስ አድን ስራው መቋረጡን ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡

የናይጄሪያ ቀይ መስቀል ዓርብ ዕለት ባወጣው መግለጫ፤ የጎርፉ አደጋው የበርካታ ሰዎች ህይወት የጠፋበት እና ንብረት የወደመበት መሆኑን አስታውቋል፡፡

ከዚህ ቀደም እ.ኤ.አ በ2024 በናይጄሪያ በከባድ ዝናብ ምክንያት የጎርፍ አደጋ ተከስቶ እንደነበር ዘገባው አስታውሷል።

በዚህም ምክንያት በርካታ ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ የአካባቢው ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለዋል።

በተጨማሪም በ2022 በሀገሪቱ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ተከስቶ የነበረ ሲሆን ይህም ከ600 በላይ ሰዎች እንዲሞቱና 1 ነጥብ 3 ሚልዮን ሰዎች እንዲፈናቀሉ ምክንያት መሆኑ ተነግሯል።

በሰፊና ሁሴን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review