በአማራ ክልል ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በርካታ ታጣቂ ቡድኖች መንግስት ያቀረበውን የሰላም አማራጭ ተቀብለው እጅ መስጠታቸዉን የአማራ ክልል ፖሊስ አስታወቀ

You are currently viewing በአማራ ክልል ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በርካታ ታጣቂ ቡድኖች መንግስት ያቀረበውን የሰላም አማራጭ ተቀብለው እጅ መስጠታቸዉን የአማራ ክልል ፖሊስ አስታወቀ

AMN ሰኔ 03/2017 ዓ.ም

በአማራ ክልል ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በርካታ ታጣቂ ቡድኖች መንግስት ያቀረበውን የሰላም አማራጭ ተቀብለው እጅ መስጠታቸዉን የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ገለጹ፡፡

ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ በተለይ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ እንደተናገሩት የክልሉ መንግስት በሰላም እጅ ለሚሰጡ ታጣቂዎች በቂ የመቀበያ ቦታዎችን አዘጋጅቷል ብለዋል።

የጥምር ጦሩ በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠናዎች ሁሉ ድልን እና ውጤትን በማስመዝገቡ አሁን ላይ አጠቃላይ በክልሉ ያለው የሰላም ሁኔታ አስተማማኝ ደረጃ ላይ ይገኛል ብለዋል።

የህገወጥ ቡድኖችን የሽብር ድርጊት እንዳይሳካ ከማድረግ ረገድ የክልሉ ህዝብ ጉልህ ድርሻ አበርክቷል ያሉት የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ በዚህም በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የሚካሄዱ ሁነቶች ያለምንም የጸጥታ ችግር እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል።

የክልሉ አጠቃላይ የሰላም ሁኔታ እየተለወጠና እየተቀየረ መሆኑም ኮሚሽነሩ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ ተናግረዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review