AMN-ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም
በምርጫው ፉክክር ዋንኛ ትኩረት የሆኑት ሰባት ግዛቶች መካከል እስካሁን የአንዱ ግዛት ብቻ ውጤት ቆጠራ ተጠናቆ ይፋ የተደረገ ሲሆን በሰሜን ካሮላይና ግዛት ዶናልድ ትራምፕ አሸንፈዋል፡፡
የዶናልድ ትራምፕ በሰሜን ካሮላይና ማሸነፍ ቁልፍ ጉዳይ ሲሆን ግዛቱ 16 ኤሌክቶራል ኮሌጅ ሲኖረው በአሁኑ ወቅት ትራምፕ በአጠቃላይ 230 ኤሌክቶራል ኮሌጅ በማግኘት ምርጫውን እየመሩ ይገኛሉ፡፡
ካማላ ሐሪስ ካሊፎርኒያን ጨምሮ በጽኑ የዴሞክራት ደጋፊ ግዛቶች ባስመዘገቡት ውጤት 182 ኤሌክቶራል ኮሌጅ በማግኘት በምርጫው እየተፎካከሩ ነው።
አሁንም ከፍተኛ የምርጫ ፉክክር እየተደረገ ያለው በአሪዞና፣ ጆርጂያ፣ ኔቫዳ፣ ሚሺጋን፣ ፔንሲልቫኒያ እና ዊስከንሰን ነው።
በአሳየናቸው ክፍሌ