በአሜሪካ እና በቻይና መካከል የንግድ ጦርነቱ ተፋፍሟል

You are currently viewing በአሜሪካ እና በቻይና መካከል የንግድ ጦርነቱ ተፋፍሟል

AMN – ሚያዝያ 2/2017 ዓ.ም

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአብዛኛዎቹ የዓለም ሀገራት ላይ የጣሉትን ቀረጥ ለ90 ቀናት ያዝ ያደረጉ ሲሆን፣ ከቻይና ጋር የገቡት የንግድ ጦርነት ግን መፋፋሙ ተገልጿል።

በአስገራሚው የፖሊሲ ለውጥ፣ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ወደ 60 በሚጠጉ የአሜሪካ የንግድ አጋሮች ላይ ቀረጥ ከጣሉ በኋላ፣ ድርድሮች መቀጠላቸውን ተከትሎ ዝቅተኛው የ10 በመቶ ቀረጥ ለጊዜው ያዝ እንዲደረግ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡

ነገር ግን በተመሳሳይ ጊዜ ከቻይና ወደ አሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ የቀረጥ ጭማሪውን ወደ 125 በመቶ ከፍ አድርገዋል፡፡

ቤጂንግ ከአሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ 84 በመቶ ቀረጥ በመጣል የአጸፋ እርምጃ በመውሰዷ ህግ አላከበረችም በሚል እዚህ ውሳኔ ላይ እንደደረሱ መገለጹን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ቀደም ሲል ፕሬዚዳንት ትራምፕ አሜሪካ የጣለችውን ቀረጥ ተከትሎ የአጸፋ እርምጃ ለመውሰድ የሚሞክር የትኛውም ሀገር ተጨማሪ ቀረጥ እንደሚጠብቀው ማስጠንቀቃቸው አይዘነጋም፡፡

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review