በአሜሪካ ፊላደልፊያ ግዛት በተከሰከሰው የህክምና አውሮፕላን የ6 ሰዎች ህይወት ሳያልፍ እንዳልቀረ ተገለጸ

You are currently viewing በአሜሪካ ፊላደልፊያ ግዛት በተከሰከሰው የህክምና አውሮፕላን የ6 ሰዎች ህይወት ሳያልፍ እንዳልቀረ ተገለጸ

AMN – ጥር 24/2017 ዓ.ም

በአሜሪካ ፊላደልፊያ ግዛት በተከሰከሰው የታካሚዎች ማጓጓዣ አውሮፕላን የበረራ ሰራተኞችን ጨምሮ የ6 ሰዎች ህይወት ሳያልፍ እንዳልቀረ ተገልጿል፡፡

በአንድ ሳምንት ውስጥ በአሜሪካ የተከሰተውን የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ሦስት ያደረሰው በፊላደልፊያ ሰሜን ምስራቅ ክፍል የተከሰከሰው አነስተኛ የታካሚዎች ማጓጓዣ አውሮፕላን፣ በህንፃዎች ላይ በመውደቁ በሥፍራው ባሉ ቤቶች እና ተሸከርካሪዎች ላይ እሳት ሲያስነሳ፣ በሰዎች ላይም ጉዳት ማድረሱ ተመላክቷል፡፡

ዓርብ አመሻሽ ላይ የተከሰከሰው ጄት አራት የአውሮፕላኑን ሰራተኞች፣ አንድ ህፃን ታካሚ እና የታካሚዋን አስታማሚ ይዞ እንደነበር የህክምና አውሮፕላን ኩባንያ የሆነው ኤየር አምቡላንስ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበረችው ልጅ ለሕይወት አስጊ ለሆነ ህመም በአሜሪካ ህክምና ተደርጎላት ወደ ሜክሲኮ በመመለስ ላይ እንደነበረችም የኩባንያው ቃል አቀባይ ለኤንቢሲ ገልጸዋል፡፡

ታካሚዋ ከእናቷ፣ ከአውሮፕላን አብራሪ፣ ከረዳት አብራሪ፣ ከዶክተር እና ድንገተኛ ህክምና እርዳታ ሰጪ ሀኪም ጋር አብረው እንደነበሩ ቃል አቀባዩ አክለው ተናግረዋል።

`

ከህመሟ ለመዳን ብዙ ስትታገል መቆየቷ የተነገረው ታካሚዋ፣ በሦስተኛ ወገን በተገኘ ድጋፍ የህክምና እርዳታ ለማግኘት ብትችልም መጨረሻዋ ግን በዚህ አሳዛኝ አደጋ ተደምድሟል ብለዋል፡፡

የፔንሲልቫኒያ ግዛት አስተዳደር ጆሽ ሻፒሮ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ክስተቱን “አሳዛኝ የአቪዬሽን አደጋ” በማለት የገለጹት ሲሆን፣ በአደጋው ብዙ ውድመት እንደሚኖር እናውቃለን ብለዋል፡፡

የድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች ወደ ሥፍራው ሲደርሱም በአካባቢው የተቀጣጠለ እሳት፣ ጎዳና ላይ የተሰበሰቡ ነዋሪዎችን እና የአውሮፕላን ስብርባሪ መመልከታቸው ነው የተገለጸው፡፡

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አደጋውን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት፣ ተጨማሪ ንፁህ ነፍሶች በመጥፋታቸው ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማቸው መግለፃቸውን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review