በአቶ ሙስጠፌ መሃመድ የተመራ የሶማሌ ክልል ልዑካን ቡድን ሠመራ ገባ

You are currently viewing በአቶ ሙስጠፌ መሃመድ የተመራ የሶማሌ ክልል ልዑካን ቡድን ሠመራ ገባ

AMN – መጋቢት 8/2017 ዓ.ም

በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ የተመራው የሶማሌ ልዑክ ሰመራ ገብቷል፡፡

በሶማሌ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ የተመራው የሶማሌ ልዑክ በሠመራ አሊሚራህ ሀንፈሬ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ፣ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሀጂ አወል አርባን ጨምሮ ከፍተኛ የክልሉ የስራ ሀላፊዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል።

የአፋርና የሶማሌ ወንድማማች ህዝቦች የኢፍጣር መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት በሠመራ ከተማ እንደሚካሄድም ተመላክቷል፡፡

በሁለቱ ህዝቦች መካካል ለሚካሄደው የኢፍጣር መርሃ ግብር ላይ ለመሳተፍ የሰላም ሚኒስትር አቶ መሀመድ እንድሪስ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሼኽ ሃጂ ኢብራሂም ቱፉ እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች እና የፌደራል መንግስት ተቋማት ሃላፊዎች ሰመራ መግባታቸውን ከአፋር መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review