በአእምሮ ጤና ላይ አተኩረዉ ከሚሰራጩ 100 የቲክ ቶክ ቪዲዮ ይዘቶች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የተሳሳተ መረጃ የያዙ መሆናቸዉን ጥናት አመላከተ

You are currently viewing በአእምሮ ጤና ላይ አተኩረዉ ከሚሰራጩ 100 የቲክ ቶክ ቪዲዮ ይዘቶች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የተሳሳተ መረጃ የያዙ መሆናቸዉን ጥናት አመላከተ
  • Post category:ጤና

AMN – ግንቦት 26/2017 ዓ.ም

በአእምሮ ጤና ላይ አተኩረዉ ከሚሰራጩ 100 የቲክ ቶክ ቪዲዮ ይዘቶች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የተሳሳተ መረጃ የያዙ መሆናቸዉን የጋርዲያን ጥናት አመላክቷል።

ማህበራዊ ሚዲያው በተለይም ቲክ ቶክ ለአእምሮ ጤና ምክር ምንጭ እየሆነ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ አብዛኛዎቹ ቪዲዮዎች አሳሳች እና ጎጂ መረጃዎችን የያዙ ናችው ሲሉ ባለሞያዎች አስጠንቅቀዋል።

ዘ ጋርዲያን በአእምሮ ጤና ላይ አተኩረዉ በተሰራጩ 100 የቲክ ቶክ ቪዲዮዎች ላይ ባደረገው ጥናት 52 የሚሆኑት ቪዲዮዎች የተሳሳተ የህክምና ቃላትን እና ያልተረጋገጡ ፈጣን መፍትሄዎችን ጨምሮ የተሳሳቱ መረጃዎችን የያዙ እንደሆኑ አረጋግጧል።

በብሪቲሽ እውቅና ያለው የሥነ ልቦና ማህበር የስነ-ልቦና አማካሪ የሆኑት አምበር ጆንስተን፤ ቪዲዮዎቹ እንደ ስነ-ልቦና ጉዳት እና የድህረ-አሰቃቂ ውጥረት ዲስኦርደር (ፒ ቲ ኤስ ዲ) ያሉ ውስብስብ የአእምሮ ጤና ጉዳዮችን አብዝተው እንደሚያቃልሉ ገልፀዋል።

ባለሞያዋ መረጃዎቹ የጤና ችግሮቹ ያሉባቸው ተመልካቾችን በማሳሳት ጉዳት ሊያደርሱ እንደሚችሉም ጠቁመዋል።

በምላሹ ቲክ ቶክ ትክክለኛ መረጃዎችን ለማስተዋወቅ ከጤና ድርጅቶች ጋር እንደሚሰራ በመግለጽ የተሳሳተ መረጃን ለመግታት ጥረት እያደረገ እንደሆነ አስታውቋል።

ዘ ጋርዲያን ያነጋገራቸው የፓርላማ አባላት እና የዘርፉ ባለሙያዎች በበኩላቸዉ የህብረተሰብን ጤና እና ደህንነት ከመጠበቅ አንፃር ጠንከር ያሉ ደንቦችን ያጠቃለለ የኢንተርኔት ደህንነት ህግ ማሻሻያ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review