
AMN ታሕሣሥ 6/2017 ዓ .ም
የመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ከአዲስአበባ የኮሪደር ልማት ቀጥሎ በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተሞች፣ በተለይ በቢሾፍቱ በአስደናቂ ጥራት እና ውበት የተሰራው መሆኑን አመልክተዋል።
የጅማ ኮሪደር ልማት፣ አዳማ፣ ሮቤ፣ አጋሮ እንዲሁም በአማራ ክልል ጎንደር፣ ባህር ዳር፣ደሴ፣ ኮምቦልቻ፤ በሲዳማ ሀዋሳ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ በአርባምንጭ እና በሌሎችም ክልሎች የኮሪደር ስራው በውጤታማነት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።
የቤንቺ ሸኮ መዲና ከላይ ከጠቀስኳቸው ከተሞች ጋር በሚመጣጠን ደረጃ የገዘፈ የኮርደር ልማትን ጀምራለች ሚዛን አማንም መሠረታዊ ጉዳዮችን ከግምት በማስገባት እሠየው የሚያሳኝ ስራ እየከወነች ነው ብለዋል።
ብርህን ያሸበረቁ ከተሞች እጅግ የዘመኑ፣ ብቁ መሠረተ ልማት ያሟሉ፣ በነዋሪዎች የሚወደዱ፣ ለኢንቨስትመንት ተማራጭ የሆኑ የመጪው ዘመን ተስፋና የብልጽግና ተምሳሌት ናቸው። የኢትዮጵያ የኮሪደር ልማትም የእነዚህን ከተሞች ፈለግ የተከተለ ነውም ብለዋል ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) በመልእክታቸው።