በአዲስ አበባ በተቋማት የቆዩ የኦዲት ጉድለት ግኝቶችን በርብርብ እንዲመለሱ ማድረግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግስት በጀት አስተዳደር እና ቁጥጥር ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ።
ቋሚ ኮሚቴው የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ ተግባራትን ምልከታ በማድረግ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀሙን ገምግሟል።
ቋሚ ኮሚቴው በከተማዋ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የሁሉም ክትትልና ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ የፋይናንስ ቢሮ ያቀረበውን ሪፖርት መነሻ በማድረግ የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች በማንሳት ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ስንታየሁ ደስታ፣ የፋይናንስ ቢሮው በጀቱን ለታለመለት አላማ እንዲሁም ለዘላቂ ልማቶች እየዋለ መሆኑን በግምገማው ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል።

በተቋማት ለበርካታ ዓመታት የቆዩ የኦዲት ጉድለት ግኝቶችን በርብርብ እንዲመለሱ ማድረግ እንደሚገባም የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ስንታየሁ ደስታ ተናግረዋል።
ኃላፊው የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ክትትልና ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን፣ ቢሮው የተለያዩ የሪፎርም ተግባራት ማከናወኑን ተናግረዋል።
ከኦዲት ጉድለት ጋር በተያያዘ በምክር ቤት የኦዲት ፎርም መቋቋሙን በማስታወስ ይህም የኦዲት ግኝት ማስመለስ የሚቻልበት ሁኔታ መፈጠሩን አመላክተዋል።
በመሀመድኑር ዓሊ