በመዲናዋ በ7 ቢሊዮን ብር የኢንዱስትሪ ክላስተር እየተገነባ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ገለጹ።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በ93 ሄክታር መሬት ላይ እየተገነባ የሚገኘው የኢንዱስትሪ ክላስተር የገቢያ ማዕከል፣ የኤግዚብሽን እና የውጭ ግብይት ሰንሰለት ያለው ዘመናው ክላስተር እንደሆነም ነው አቶ ጃንጥራር የገለጹት፡፡
ክላስተሩ ሲጠናቀቅ በርካታ ኢንዱስትሪዎች በቀጣይ በሚዘጋጀው የመመልመያ መስፈርት መሰረት ወደ ክላስተሩ እንደሚገቡም ጠቁመዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአምራች ኢንዱስትሪውን ምርታማነት ለማሳደግ ምቹ ምህዳር እየተፈጠረ ስለመሆኑ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡