በአዲስ አበባ ከተማ ለዓይን የማይመቹ እና ለአፍንጫ የሚሰነፍጡ አካባቢዎች አሁን ላይ በአረንጓዴ ልማት ስራዎች ተቀይረዋል-የአዲስ አበባ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ

You are currently viewing በአዲስ አበባ ከተማ ለዓይን የማይመቹ እና ለአፍንጫ የሚሰነፍጡ አካባቢዎች አሁን ላይ በአረንጓዴ ልማት ስራዎች ተቀይረዋል-የአዲስ አበባ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ

AMN- ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ ለዓይን የማይመቹ እና ለአፍንጫ የሚሰነፍጡ አካባቢዎች አሁን ላይ በአረንጓዴ ልማት ስራዎች ተቀይረዋል-የአዲስ አበባ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ገለጹ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የለሙ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች በዘላቂነት እንዲቀጥሉ ለማድረግ ሚያስችል የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ተካሄደ።

አዲስ አበባ ከተማን እንደ ስሟ ውብ ለማድረግ እየተሰሩ ባሉ ተግባራት የአረንጓዴ ልማት ስራዎች ትኩረት ተሰጥቷቸዋል።

በተለይም በኮሪደር ልማቱ በርከት ያሉ የከተማዋ ክፍሎች በአረንጓዴ እጽዋቶችና ዛፎች ተሸፍነዋል።

የመዝናኛ ፖርኮች በመንገድ አካፋዮች የተሰሩ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች በዘላቂነት ለትውልድ እንዲሻገሩም በባለቤትነት ለሚንከባከቡና ለሚያለሙ ማህበራት ተላልፈዋል።

“የአረንጓዴ ልማት ሰራዊት” የሚል ስያሜ ለተሰጣቸው ተንከባካቢዎች የርክክብ ስነ ስርዓትና የህዝብ የንቅናቄ መድረክ የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት አዲስ አበባ ከተማ መገለጫዋ እስኪመስሉ ድረስ ለአይን የማይመቹ ፤ለአፍንጫ የሚሰነፍጡ የነበሩ አካባቢዎች በአረንጓዴ ልማት ስራዎች አሁን ላይ ተቀይረዋል።

በመጀመሪያው ዙሪ የኮሪደር ልማት ብቻ 60 ሄክታር መሬት በአረንጓዴ እጽዋትና ዛፎች መሸፈናቸውን ገልጸው ከ70 በላይ የሚሆኑ የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጡ የህዝብ መናፈሻዎች እና 38 የውሀ አካላት ለምተዋል ብለዋል።

እነዚህን ውብ የከተማዋን ክፍሎችም በዘላቂነት ለትውልድ ለማስተላለፍ ለ4ሺ ተንከባካቢዎችና ለሺ አልሚዎች በባለቤትነት ተላልፈዋል ነው ያሉት ።

ሀላፊነት የተሰጣቸው እነዚሁ ተንከባካቢና አልሚ ማህበራትም የተጣለባቸውን አደራ በአግባቡ ሊወጡ ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል።

በህዝብ ንቅናቄ መድረኩ ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች ለተመረጡ ተጽእኖ ፈጣሪና ታዋቂ ግለሰቦችም የአረንጓዴ ልማት አምባሳደርነት ተሰጥቷል።

በፍቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review