በአዲስ አበባ ከተማ በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በመገንባት ላይ የሚገኙ ፕሮጅክቶች ግንባታ እየተፋጠነ መሆኑ ተገለጸ

You are currently viewing በአዲስ አበባ ከተማ በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በመገንባት ላይ የሚገኙ ፕሮጅክቶች ግንባታ እየተፋጠነ መሆኑ ተገለጸ

AMN – ሚያዝያ1/2017 ዓ.ም

በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በመገንባት ላይ የሚገኙ ፕሮጅክቶች የግንባታ ሂደት እየተፋጠነ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ፕሮጀክቶቹ በዓለም ባንክ የልዑክ ቡድን ተጎብኝተዋል፡፡

የጉብኙቱ ዓላማ በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በመገንባት ላይ የሚገኙት የኮዬ ፈጬ፣ የኪቲሜ፣ የኮተቤ የፍሳሽ ማጣርያ ጣቢያዎች እንዲሁም የአራብሳ የሳኒተሪ ላንድፊል እና የከፍተኛ ፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክቶች ያሉበትን የግንባታ ሂደት ለማወቅ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የቻይና ተቋራጭ በሆነው የCGCOC ድርጅት የሚገነባው የኮዬ ፈጬ የፍሳሽ ማጣርያ ጣቢያ በቀን 20,050 ሜትር ኪዩቢክ ፍሳሽ የማጣራት አቅም እንደሚኖረው የተጠቆመ ሲሆን፣ ግንባታው በ22 ወራት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ወደ ስራ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

በተያያዘም የቀድሞውን ዲዛይን በማሻሻል የሽታ ማስወገጃ፣ ተጨማሪ ፓንፕ እና ስታንድባይ ጅነሬተር እንዲገጠምለት መደረጉ የአካባቢውን ነዋሪ ከብክለት መከላከል እንዲሁም የማጣርያ ጣቢያው የበለጠ እንዲዘምን መደረጉ በጎብኚዎቹ አድናቆት ተችሮታል፡፡

የኮተቤ ፍሳሽ ማጣርያ ጣቢያም በአጠቃላይ ፕሮጅክቶቹ ጥሩ የአፃፀም ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የተመላከተ ሲሆን፣ አንዳንድ የሚስተዋሉ ችግሮችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር መፍታት እንደሚገባ በጉብኝ ቡድኑ አቅጣጫ መሰጠቱን ከአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review