በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ቀናት በነዳጅ ማደያዎች አካባቢ የታዩት ረዣዥም ሰልፎች የነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች በፈጠሩት የስርጭት ችግር መከሰቱን የከተማዋ ንግድ ቢሮ አስታወቀ።
በከተማዋ ሆን ተብሎ የነዳጅ ስርጭት ችግር እንዲፈጠር በሚያደርጉ አካላት ላይም እርምጃ እንደሚወስድ የቢሮው ሀላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ከኤ ኤም ኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል።
የነዳጅ ማደያዎች የነዳጅ ፍላጎት ልክ ለኩባንያዎች ያቀረቡ ሲሆን ኩባንያዎቹ ግን በተቃራኒው ለነዳጅ ድርጅት በስርዓቱ አለማቅረብ ታይቷል ነው ያሉት።
ኩባንያዎቹ ጋር የመንግስትን አቅጣጫ እስካለመቀበል የሚደርሱ ችግሮችም እንደተስተዋሉም ጨምረው ተናግረዋል።
የነዳጅ ኩባንያዎቹ በፈጠሩት የስርጭት ችግር ባለፉት ቀናት ከሚፈለገው ናፍጣ 20 በመቶ ብቻ አዲስ አበባ የገባ ሲሆን አሁን ላይ 65 በመቶ መድረሱንም ጠቅሰዋል።
በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ደግሞ የሚፈለገውን የነዳጅ መጠን በማስገባት ችግሩን ሙሉ በሙሉ ለመቅረፍ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በሚቀጥሉት ጊዜያት ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይከሰቱ የቁጥጥር ስራውን ለማጥበቅ እና እርምጃ ለመውሰድ እንደሚሰራም ገልጸዋል።
ለዚህም በቅርቡ የወጣው የነዳጅ ግብይት አዋጅ እና የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለቁጥጥሩ የሰጠው ፈቃድ አጋዥ መሆኑን አንስተዋል።
ሀላፊዋ ማህበረሰቡ በነዳጅ ስርጭት እና ንግድ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ህገወጥ ተግባራትን ከመከላከል አንጻር የበኩሉን እንዲወጣም ጠይቀዋል።
በአፈወርቅ አለሙ


All reactions:
142Mehretu Fekade, Muluken Getnet and 140 others